የባህል ሕክምናና የሐኪም መድኃኒትዎ
Traditional medicine and your prescriptions
በሐኪም (MD) የተጻፈ · Written by an MD · 2026-09-20
ምንድን ነው?
የባህል ሕክምና (traditional medicine) የአያቶቻችን እውቀት ነው። ዳማከሴ ለጉንፋን፣ ጤናዳም ቡና ውስጥ፣ ኮሶ ለሆድ ትል፤ በብዙ የኢትዮጵያ ቤት ውስጥ የተለመዱ ናቸው። ብዙ ዘመናዊ መድኃኒቶችም ከፕላንት (plant) ነው የመጡት፤ አስፕሪን (aspirin) ከዊሎው ዛፍ ቅርፊት፣ የወባ መድኃኒት አርቲሚሲኒን (artemisinin) ከቻይና ፕላንት። WHO።
ስለዚህ «ከፕላንት ነው» ማለት «ደካማ ነው» ማለት አይደለም። ግን «ናቹራል (natural) ነው» ማለት «ሴፍ (safe) ነው» ማለትም አይደለም። ፕላንት ማለት ኬሚካል (chemical) ማለት ነው። ልዩነቱ አንድ ነው፤ ኪኒን ውስጥ ዶዙ (dose) ተለክቷል፣ ቅጠል ውስጥ ዶዙ እንደ ዝናቡ፣ እንደ አፈሩ፣ እና እንደ ማን እንዳዘጋጀው ይለያያል። የሄርባል (herbal) ምርቶች እንደ መድኃኒት ተፈትነው አይደለም የሚሸጡት። MedlinePlus።
ችግሩ ያለው ቅጠሉና የሐኪም መድኃኒትዎ ሲገናኙ ነው። ሁለቱም ወደ ሊቨር (liver) ይሄዳሉ። ሊቨር ውስጥ ያሉ ኤንዛይሞች (enzymes) መድኃኒቱን ሰብረው ከሰውነት ያስወጡታል። አንዳንድ ሄርቦች ይህን ሥራ ያፋጥናሉ፤ መድኃኒቱ ቶሎ ይወጣል፣ ብለድ ፕሬሸርዎ (blood pressure) ወይም ስኳርዎ ወደ ላይ ይሄዳል። ሌሎች ደግሞ ስሎው (slow) ያደርጋሉ፤ መድኃኒቱ ይከማቻል፣ ዶዙ ከሚገባው በላይ ይሆናል። እዚህ አሜሪካ ግሬፕፍሩት (grapefruit) ጁስ ከብዙ መድኃኒት ጋር «አትጠጡ» የሚባለው ለዚህ ነው። NIH NCCIH።
አደገኛ ምልክቶች
ከሚከተሉት አንዱ ካለ ወዲያውኑ እርዳታ ይፈልጉ፦
- ዓይን ወይም ቆዳ ቢጫ መሆን (jaundice)።
- ጠቆር ያለ ሽንት ወይም ነጣ ያለ ሰገራ።
- የቀኝ ላይኛው ሆድ ሕመም ከማቅለሽለሽ፣ ከማስታወክ ወይም ከከባድ ድካም ጋር።
- የማይቆም መድማት፣ ጥቁር ሰገራ፣ ወይም ደም ማስታወክ።
- ራስን መሳት፣ ግራ መጋባት፣ ወይም ድንገተኛ የዓይን ብዥታ።
እነዚህ የሊቨር ጉዳት (liver injury) ወይም የከባድ መድማት ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። አዲስ ኪኒን፣ ሻይ ወይም ሱፕልመንት ከጀመሩ በኋላ ከመጡ፣ አይጠብቁ። በአሜሪካ 911 ይደውሉ፤ በአዲስ አበባ የቀይ መስቀል አምቡላንስ 907፤ በሌላ አገር የአካባቢዎን የድንገተኛ እርዳታ ያነጋግሩ። MedlinePlus።
ቤት ውስጥ ምን ማድረግ?
- ከአገር ቤት የመጣውን ፓኬጅ (package) ራሱ ይዘው ወደ ሐኪምዎ ወይም ወደ ፋርማሲስትዎ (pharmacist) ይሂዱ። ጀጅ (judge) አያደርጉዎትም፤ ሥራቸው ነው። ፋርማሲስት ኢንተራክሽን (interaction) ቼክ ማድረግ በነጻ ይችላል።
- በምግብ መጠን ያለውን ቅመም አይፍሩ። ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ምግብ ላይ ሲሆኑ ሄልዚ (healthy) ናቸው። ችግሩ ያለው ወፍራም ሻይና ሱፕልመንት ላይ ነው። NIH NCCIH።
- ዳማከሴ በትንሽ መጠን ለጉንፋን በአብዛኛው ችግር የለውም። ትኩሳቱ ግን የማይወርድ ከሆነ፣ ሻይ አይበቃም፤ ሐኪም ያስፈልጋል።
- ጤናዳም ቡና ውስጥ አንድ ቅጠል ፍሌቨር (flavor) ነው። ወፍራም የጤናዳም ሻይ ተደጋግሞ አይጠጡ። ፕሬግናንት (pregnant) ከሆኑ፣ ከቡናዎ ፍሌቨር ውጭ አይውሰዱ።
- ኮሶ ደካማ ወይም ጠንካራ ሊሆን ይችላል፤ ዶዙ አይታወቅም። ለሆድ ትል ዶዙ የተለካ የሐኪም ኪኒን አለ።
- የታዘዘልዎትን መድኃኒት በራስዎ አያቁሙ። ኢንሱሊን (insulin)፣ የቲቢ (TB)፣ የኤች አይ ቪ (HIV) ወይም የካንሰር (cancer) ሕክምና በቅጠል አይተካም። ቅጠል ከመድኃኒትዎ ጋር ከመውሰድዎ በፊት ሐኪምዎን ወይም ፋርማሲስትዎን ያማክሩ፤ ከመድኃኒት ጋር ሊጋጭ ይችላል።
- ጸበል፣ ዘምዘም፣ ዱዓና ጸሎት የእምነት ጉዳዮች ናቸው። ሕክምና አይተካቸውም፣ እነሱም ሕክምናን አይተኩም። ችግሩ የሚመጣው አንዱ ሌላውን ሲተካ ነው።
ምልክቶች
የባህል መድኃኒትና የሐኪም መድኃኒት ሲጋጩ ሰውየው የሚያስተውለው፦
- መድኃኒቱ «እንደ በፊቱ አይሠራም»፤ ብለድ ፕሬሸር ወይም ስኳር ያለምክንያት ወደ ላይ ይሄዳል።
- ወይም ደግሞ መድኃኒቱ «በጣም ይሠራል»፤ ራስ ማዞር፣ ድካም፣ ስኳር ወደ ታች መውረድ።
- ብለድ ቲነር (blood thinner) ከሚወስዱ፣ በቀላሉ መድማት፣ ድድ መድማት፣ ያለምክንያት ሰማያዊ ምልክት በቆዳ ላይ።
- ወፍራም ሻይ ወይም ሱፕልመንት (supplement) ከጀመሩ በኋላ የመጣ የሆድ ሕመም፣ ማቅለሽለሽ ወይም ማሳከክ።
- ኮሶ በብዛት ሲወሰድ፣ ራስ ማዞር፣ ራስን መሳት፣ የዓይን ችግር።
ሐኪም መቼ ማየት?
- ብለድ ቲነር፣ የስኳር መድኃኒት፣ የሚጥል በሽታ መድኃኒት፣ ወይም የሊቨር ወይም የኪድኒ (kidney) በሽታ ካለዎት፣ ማንኛውንም ሄርብ ከመጀመርዎ በፊት ሐኪም ይጠይቁ።
- ሰርጀሪ (surgery) እየተዘጋጁ ከሆነ፣ የሚወስዱትን ሁሉ አስቀድመው ይንገሩ። አንዳንድ ሱፕልመንቶች መድማት ይጨምራሉ ወይም አኔስቴዥያን (anesthesia) ይነካሉ። NIH NCCIH።
- ፕሬግናንት ከሆኑ ወይም ጡት እያጠቡ ከሆነ፣ ማንኛውም ሻይ ወይም ቅጠል ከመውሰድዎ በፊት ይጠይቁ።
- መድኃኒትዎ የተለመደውን ውጤት ካልሰጠ፣ ወይም አዲስ ቅጠል ከጀመሩ በኋላ አዲስ ምልክት ከመጣ፣ በቅርቡ ያስመርምሩ።
- ትኩሳት፣ ራስ ምታት ወይም የሆድ ሕመም በባህል መድኃኒት እየታከመ ካልሻለ፣ ጊዜ አያባክኑ። መዳን የሚችል በሽታ ሲዘገይ ከባድ ይሆናል።
መከላከያ
- ለእያንዳንዱ ሐኪምና ፋርማሲስት የሚወስዱትን ሁሉ ይንገሩ፤ ኪኒንም፣ ቅጠልም፣ ሱፕልመንትም። ዝርዝሩን ስልክዎ ላይ ይያዙ።
- ከውጭ የሚመጡ አንዳንድ የባህል መድኃኒቶች ውስጥ ሊድ (lead) እና ሜርኩሪ (mercury) ተገኝቷል፤ ሌሎች ውስጥ ደግሞ ማሸጊያው ላይ ያልተጻፈ መድኃኒት ወይም ስቴሮይድ (steroid) ይገኛል። ምንጩ ያልታወቀ ምርት አይግዙ። NIH NCCIH።
- «ናቹራል» የሚል ሌብል (label) ኢቪደንስ (evidence) አይደለም።
- ልጆች ላይ የሚደረጉ የባህል ድርጊቶች፣ እንጥል መቁረጥና የወተት ጥርስ ማውጣት፣ መድማትና ኢንፌክሽን (infection) ሊያመጡ ይችላሉ። ቤቢዎን ይዘው ወደ አገር ቤት ሲሄዱ፣ ይህን አስቀድመው ይወስኑ።
- ቅጠል ወይም ሻይ ሲጠቀሙ በምግብ መጠን ይሁን፤ በየቀኑ ወፍራም ሻይ አይሁን።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
- ይህ ቅጠል ወይም ሻይ ከመድኃኒቴ ጋር ይጋጫል?
- መድኃኒቴ ሊቨሬን ይነካል? የሊቨር ቴስት ያስፈልገኛል?
- ሰርጀሪ ወይም ፕሬግናንሲ ካለ፣ ምን ማቆም አለብኝ፣ መቼ?
- ፋርማሲስቱ የኢንተራክሽን ቼክ እንዲያደርግልኝ እንዴት እጠይቃለሁ?
ምንጮች
- NIH NCCIH. Using Dietary Supplements Wisely.
- MedlinePlus. Herbal Medicine.
- MedlinePlus Medical Encyclopedia. Drug-induced liver injury.
- WHO. Traditional medicine: questions and answers.
ጥያቄዎችና መልሶች · 4
ከርቤ ይጠጣል ወይ?
የሚቀባው ዘይት ለቆዳ ብቻ ነው፣ አይጠጣም። ከርቤን መጠጣት በብዛት ሲሆን ሆድ ሊያቃጥልና ተቅማጥ ሊያመጣ ይችላል፤ ነፍሰ ጡር ሴት ደግሞ ጭራሹን መውሰድ የለባትም።
በአማራ ክልል "ትርፍ ምላስ" እየተባለ ከ3 ወር ልጅ ጀምሮ ከአንገታቸው ሥር ይተኮሳሉ፤ ሁሉም ሕፃናት።
እውነት ነው፣ ትርፍ ምላስ የሚባል በሽታ የለም። መተኮስ ምንም አይፈውስም፣ ይልቁንም ጠባሳና ኢንፌክሽን ያመጣል፣ በጨቅላ ህፃናት ደግሞ አደገኛ ነው። ልጁ ምራቅ ቢያዝረከርክ ወይም ጡት ቢከብደው መንስኤው ታይቶ የሚታከም ነው።
ለግፊት ጥሩ ብለዉኝ በቀረፋ ተዘፍዝፎ አድሮ እየጠጣሁ ነዉ ጉዳት ይኖረዉ ይሆን ?
ቀረፋ በሻይ መጠን መጠጣት ለአብዛኛው ሰው ጉዳት የለውም፤ ግን የደም ግፊትን እንደሚያክም የሚያሳይ በቂ ማስረጃ የለም። በገበያ የተለመደው የቀረፋ ዓይነት በብዛትና በየቀኑ ለረጅም ጊዜ ሲጠጣ ጉበትን ሊጎዳ የሚችል ንጥረ ነገር አለው። የምንመክረው በመጠኑ እንዲጠጡት፣ የግፊት መድኃኒት ካለዎት እንዳያቋርጡና ግፊትዎን መለካት እንዲቀጥሉ ነው።
እኔ ባለዉበት ኣከባቢ ህፃናት የ ጉሮሮ ቶንስል ሰይዛቸው ህክምና ከመዉሰድ ይልቅ በ ሀበሻ መዳኒት እና እናቶች በ ማንካ ነው ሚፍቁት እስቲ እሄን ምን ትላለ ?
ልጁ መተንፈስ ካቃተው አሁኑኑ፣ መዋጥ ወይም መጠጣት ካቃተው ደግሞ ዛሬውኑ ሐኪም ቤት ይውሰዱት። ቶንሲልን በማንካ መፋቅ አያድንም፤ ቁስል፣ መድማትና ኢንፌክሽን ሊያመጣ ስለሚችል አንመክረውም። ብዙ የልጆች የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ስለሚመጣ በጥቂት ቀናት በራሱ ይሻላል። ትኩሳት ኖሮ ሳል ከሌለ ግን በባክቴሪያ ሊሆን ይችላል፤ ካልታከመ አልፎ አልፎ ልብን ሊጎዳ ስለሚችል በአንድ ወይም በሁለት ቀን ውስጥ እንዲመረመር እንመክራለን።
ተያያዥ ርዕሶች
በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን
የጉበት በሽታ
የደም ግፊት
የአንጀት ትሎች፣ የትል መድኃኒትና ንጽህና
የተለመዱ የሕክምና ምርመራዎችን መረዳትና ለክሊኒክ ጉብኝት መዘጋጀት